Saturday, 2 January 2016


አልዛይመር

አብሮ አደጌ ወዳጄ
ታምሩን በድንገት አግኝ ቼ


"ታምሩ!" ብዬ ተጣራሁኝ



አይኑን አፍጥጦ ቃኘኝ


"ማነህ " ብሎ ጠየቀኝ
መነጽሩን አስትካክሎ
 አትኩሮ አያየኝ

"የገዛ ባልንጀራህ'ኮ  ነኝ
አንዴ! ታምሩ ፣ ረሳከኝ  ?"

"አረ ታምርህን ያጥፋው "
"የት የምታቀኝን ነው  "
አለኝ
ቡጥ ይዞ  ሊነርተኝ
አየተዘጋጀብኝ

"በል ጌታ ይማርህ: አንተ  ድንጋይ ራስ  "
"ዲያብሎስ ሰርቆታል አይምሮህንስ

"በልተን ጠጥተን 
አብረን  አድገን
ጠጠር ተጫውተን
ጭ ቃ አብኩተን
"የት የምታውቀኝ ን
ነው ትለኛለ ህን?'

"በል ጌታ ይማርህ: አንተ  አይምሮ ቢስ   "
"ዲያብሎስ ሰርቆታል ሕሊናህንስ 

የታምሩ ነገር ደንቆኝ
ራሴን አያወዛወዝኩኝ
ስባክን  ያየችኝ
ቤቴ  ጽርስ ገብታ ተከትላኝ
"አንዴት  አረፈድክ" አለችኝ
"የገዛ ወዳጄ አላውቅህም ብሎኝ
ድራሸህ ይጥፋ ብሎ አባረረኝ
ምነው ሰው ሁሉ አይምሮ ቢስ ሆነብኝ

ከንፈሮቿን መጣ ተጠጋችን
ከኪሷ ኪኒን አውጥታ ሰጠችኝ
 ውሃም ኩባያ ሞልታ አያቀበለችኝ
"መድኃኒህን አትርሳ" አለችኝ